የትራምፕን ንግግር በመቃወም ኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ዛሬ ጀመረች

የትራምፕን ንግግር በመቃወም ኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ዛሬ ጀመረች

WASHINGTON, DC - OCTOBER 23: U.S. President Donald Trump speaks with Israeli Prime Minister Benjamin Netanyau on the phone about a Sudan-Israel peace agreement, in the Oval Office on October 23, 2020 in Washington, DC. President Trump announced that Sudan will start to normalize ties with Israel. Win McNamee/Getty Images/AFP

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳዋለች የሚልና የህዳሴው ግድብን ሀገራዊ ጥቅም የሚያጣጥሉ አስተያየቶች የሰጠቱት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በመቃወም ኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ልትጀምር መሆኑ ተሰማ።

ይህ ፊርማ የማሰባሰብ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ጥቅምት 21/ 2013 ዓ.ም በግዮን ሆቴል 10 ሰዐት ላይ እንደሚጀመርም በዋነኝነት ይህንን ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ የሚመራው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የጽሕፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም፤ ፊርማው በበይነ መረብ (ኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን፣ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳዋለች ለሚለው አፀፋዊ የተቃውሞ ምላሽ መሆኑም ተገልጿል።
ከዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ዐራት ቀናት ኢትዮጵያውያን የፕሬዚዳንቱን ንግግር ፊርማቸውን በማኖር እንዲቃወሙ ጥሪ የቀረበላቸው ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ለሚመለከታቸው ሀገራት ደግሞ ትኩረት እንዲሰጡትም ያለመ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በእነዚህ ዐራት ቀናት ውስጥ እስከ 150 ሺኅ ፊርማ የማሰባሰብ እቅድ መያዙን የጠቆሙት አቶ አለሙ፤
በተለያዩ ሀገራት በርካታ ሰዎችም በቡድን ሆነ በተናጠል የተቃውሞ ፊርማዎችን ማሰባብ መጀመሩን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፤ የሕዝብ ጥያቄ አይሎ በመምጣቱና ጽሕፈት ቤቱም ሕዝባዊ ተሳትፎ በቀጥታ የሚመለከተው በመሆኑ አንድ ወጥ በሆነና የበለጠ በተጠናከረ መልኩም ለማገዝም መታቀዱን ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያደረጉት ንግግር ፀብ ጫሪ ነው ያሉት የአዘጋጅ ቡድኑ ዋና ዳይሬክተር፣ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ የዓለም ሰላም ወዳድ ሕዝቦችም በዚህ ሊሳተፉ እንደሚችሉም ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
“ሓላፊነት የጎደለው፣ ግልፅ የሆነ ለአንድ ወገን ያዘነበለና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚነካና የሚሸረሽር ነገር ተናግረዋል። ይህም ንግግር በሀገር ውስጥም ሆነ በተለያየ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ዳር እስከ ዳር አስቆጥቷል” ያሉት አመራሩ፤ ንግግራቸው በአፍሪካም ሆነ በቀጠናው ያለውን ሰላም የሚያናጋ መሆኑን ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY