የትግራይ ህዝብ ቀናኢ ኢትዮጵያዊነትን በማረጋገጥ ታሪክ እንዲያድስ ዶ/ር አብርሃም በላይ አሳሰቡ

የትግራይ ህዝብ ቀናኢ ኢትዮጵያዊነትን በማረጋገጥ ታሪክ እንዲያድስ ዶ/ር አብርሃም በላይ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አባልና የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አብርሃም በላይ ታሪክ አጥፊ የሽሽት ቡድን ነው ያሉት ህወሓት በሀገር ላይ የቃጣውን የክህደት ተግባር መላው የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ኃይልና ከመላው የኢትዮጵያ ሕዞቦች ጋር በጋራ በመቆም በፅናት እንዲመክት ጥሪ አቀረበ።

ሀገር ወዳዱ የትግራይ ሕዝብ የክህደት ተግባሩን በጥብቅ  በማውገዝ፣ ቀናዒ ኢትዮጵያዊነትን በድጋሚ በማረጋገጥ ታሪክ እንዲያድስም ከፍተኛ አመራሩ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በሀገራችን ባለፋት ሁለት ዓመታት ተኩል የተከሰተውን ሠፊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ በልዩ ልዩ የሀገራችን ክፍሎች በተነሱ በርካታ ግጭቶች ውስጥ በስውርም ሆነ በግልጥ በአፍራሽ ተልእኮ እጁን ሲያስገባ የቆየው  የህወሓት ጠላፊ ቡድን፤ በትናንትናው ምሽት የትግራይ ሕዝቦች  ደጀን በመሆን ለዓመታት ዋጋ እየከፈለ ባለው የሀገር የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ በወሰደው አሳፋሪ የጥቃት ትንኰሳና ዝርፊያ ፌደራል መንግሥት ጠንካራ ህግ የማስከበር እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን ገልጸዋል።
“ይህ በአይነቱና በታሪክም ፍፁም እንግዳ የሆነ የክህደት ተግባር ለሀገራቸው አንድነትና ክብር ለዓመታት መስዋዕትነት ለከፈሉ ሕዝቦች ጠላፊ ቡድኑ ያለውን ንቀት ያሳየበት፣ በዚህ የለየለት እብደቱም የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ አስፈላጊው  ህጋዊ እርምጃዎች በሙሉ እየተወሰዱ ይገኛሉ ” ያሉት ዶክተር አብርሃም፤
ሰላማዊው የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያም በፌደራል መንግሥቱ እና በአማራ ክልል መንግሥት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት በመቀበል በአጎራባች የአማራ ክልሎች በመሻገር  ወንድሙ ከሆነው የአማራ ሕዝብ ጋር በሰላም እንዲቀላቀል አደራ ብለዋል።

LEAVE A REPLY