ጀነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ 3 ጀነራሎች መከላከያውን እንዲቀላቀሉ ዶ/ር ዐቢይ አዘዙ

ጀነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ 3 ጀነራሎች መከላከያውን እንዲቀላቀሉ ዶ/ር ዐቢይ አዘዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጦር ሜዳ ጀግናው ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ የውጊያ ልምድ ያላቸው ሦስት ጀነራሎች መከላከያ ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ በዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ ቀረበላቸው።

በህወሓት/ኢሐአዴግ የሥልጣን ዘመን ከመከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ መኮንኖች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ትእዛዝ መሰጠቱንና እነርሱም መቀበላቸው እየተነገረ ነው።
ዳግም የተጠሩት መኮንኖች ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ፣ ሌ/ጀነራል ዬሐንስ ገ/መስቀልና ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
እነዚህ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የጦር ጀነራሎች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲቀላቀሉ የተደረገው በትግራይ ክልል የሚገኘውን የሰሜን ዕዝን በልዮ ሁኔታ ለማዋቀርና ጦሩንም የበለጠ ለማጠናከር ታሳቢ እንደሆነ ተገምቷል።
ቆፍጣናው የጦር መሪ ጀነራል አበባው ታደሰ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ኢታማዦር ሹም የነበሩት ጀነራል ሳዓረ መኮንን ከተገደሉ በኋላ መከላከያ ሠራዊቱን በተለያየ መንገድ የማዋቀር ሥራ ሢሠራ ከጀርባ ሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያማክሩ መቆየታቸውን ምንጮቻችን ለኢትዮጵያ ነገ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY