ተጨማሪ ሠራዊት ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ መጀመሩን ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ

ተጨማሪ ሠራዊት ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ መጀመሩን ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በትግራይ ክልል ከህወሓት ጋር እየተደረገ ለሚገኘው ውጊያ ተጨማሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ጦርነቱ ቀጠና እየተንቀሳቀሱ ናቸው ተባለ።

“ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላሰበችው ጦርነት ውስጥ ገብታለች፤ ጦርነቱ አሳፋሪ ነው ፣ ዓላማም የሌለው ነው” ሲሉ መግለጫ የሰጡት ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፤ የመከላከያ ኃይል ጦርነቱን እንደሚመክተውና ጦርነቱ የትም የሚደርስ አይደለም ብለዋል።
 እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ወደ መሀል ሀገር እንደማይመጣ እና እዛው እንደሚያልቅ ያረጋገጡት ጀነራል ብርሃኑ፤ ሠራዊቱ ዳግም ጦሩን በተቀላቀሉ አዛዦች ልምድ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚሆንም አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY