ጀነራል ባጫ ደበሌ ያለጊዜዬ ጡረታ ያስወጣኝ የማፊያ ቡድን የሆነው ወያኔ ነው አሉ

ጀነራል ባጫ ደበሌ ያለጊዜዬ ጡረታ ያስወጣኝ የማፊያ ቡድን የሆነው ወያኔ ነው አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መከላከያ ሠራዊቱን የተቀላቀሉት ጀነራል ባጫ ደበሌ በቀረበላቸው ሀገራዊ ጥሪ መሠረት ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ከጥፋት ቡድኖች ለመከላከል ዝግጁ መሆናቸውንም ገለፀዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ጥሪ ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ ከተደረጉት አንጋፎቹ የጦር ጀነራሎች መሀል አንዱ የሆኑት ጀነራል ባጫ ደበሌ በህወሓት መራሹ መንግሥት የተገፉ የጦር ሜዳ ሰው መሆናቸው አይዘነጋም።
ጀነራሉ በኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውና የኢትዮ ኤርትራ ጦርነትንም በመምራት ጉልህ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ቢሆንም አምባገነኑ ቡድን ግን የዘር ሀረጋቸውን መሠረት በማድረግ በኦነግነት ተጠርጥረው ከሠራዊቱ እንዲቀነሱ አድርጓል።
 ጀነራል ባጫ ደበሌ ትናንት ማምሻውን ከOBN ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ፤ “በዚህ ሀገራችን ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት መንግስት ጥሪ ስላደረገልኝ ፈጣሪዬን ከልብ አመሰግነዋለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።
ጥሪው በሕይወቴ አዲስ ነገር ነው፤ መንግሥት ጥሪ ስላደረገልኝም ደስተኛ ነኝ ያሉት ጀነራል ባጫ ደበሌ፤ “እኔ ጡረታዬ ሳይደርስ ጡረታ እንድወጣ ያደረገኝ የማፊያ  ግሩፕ የሆነው ወያኔ ነበር። አሁን ለምወደው ሕዝቤ እና ሀገሬ ማገልገል በመጀመሬ እድለኛ ነኝ” ብለዋል።

LEAVE A REPLY