ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ህወሓት የጀመረውን ጦርነት የተቃወሙና ከወገኖቻችን ጋር አንዋጋም ያሉ 37 የታጠቁ የትግራይ ሚሊሺያ አባላት እጅ መስጠታቸው ታወቀ።
ከእነዚህ ሚሊሺያዎች በተጨማሪ 27 የታጠቁ ሌሎች የህወሓት ጀሌዎችም በተመሳሳይ ለመከላከያ ሠራዊቱና ለአማራ ልዮ ኃይል እጅ ሰጥተዋል።
ከታጣቂዎቹ በተጨማሪ የትግራይ ክልል መንግሥት ንብረት መሆኑ የተረጋገጠ ፓትሮል 3F መኪናም አብሮ ወደ ፌደራል መንግሥቱ ገቢ ሆኗል።
የሚሊሺያ አባላቱንና ሌሎች ጀሌዎችን ለውጊያ ከተሰጣቸው መሣሪያና መኪና ጋር ወደ ምዕራብ አርማጭሆ አብርጅሀጅራ ከተማ የፀጥታ ኃይሉ ይዟቸው መምጣቱም ተረጋግጧል።
ህወሓት በተለያዮ የትግራይ ክልል ለጦርነት ተሠማርተው ከነበሩ ታጣቂዎች መሀል በርካቶቹ በድንበር አካባቢ ለሚገኘው የኤርትራ ጦር እጃቸውን በመስጠት ላይ መሆናቸውን የሚያሳዮ መረጃዎችም እየወጡ ነው።