በነዳጅ ምርቶች ላይ አዲስ የግብይት ሰዐት ገደብ ወጣ

በነዳጅ ምርቶች ላይ አዲስ የግብይት ሰዐት ገደብ ወጣ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በነዳጅ ምርቶች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን ከፍተኛ ፍላጎትና ሕገ ወጥ አሠራር ተከትሎ የሽያጭ ሰዐት ገደብን የተመረኮዘ አዲስ መመሪያ መውጣቱ ተሰማ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የኮሚኒዮኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክተር ወንድሙ ፍላቴ፤ የነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭት እና ግብይትን በጥብቅ ለመከታተል እና ለመቆጣጠር እንዲቻል በሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ ጀምሮ የሰዐት ገደብ መቀመጡን ይፋ አድርገዋል።
በመሆኑም በሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ  ጀምሮ ጠዋት ከ12፡00 ሰዐት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዐት ድረስ ብቻ ነዳጅ እንደሚሸጥ ተጠቃሚዎች ሊያውቁት ይገባል ተብሏል።
በተጨማሪም በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከጧቱ 12፡00 ሰዐት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዐት ብቻ እንዲሠሩ ውሳኔ መተላለፉን ሓላፊው አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY