ጽንፈኛውን ኃይል በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ለማዋል መከላከያ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ...

ጽንፈኛውን ኃይል በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ለማዋል መከላከያ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሠራዊታችን ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ ጀነራል መሀመድ ተሰማ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያን እድገት የማይፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች የህዳሴ ግድባችንን እንዳያደናቅፉ የሀገራችን የፀጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ በቆሙበት በአሁኑ ሰዐት፣ የእናት ጡት ነካሾች ሀገራችንን በመድፈር ውጊያ ከፍተውብናል ሲሉም አዛዡ ተናግረዋል።
“ይህ ጦርነት ሀገርን ለውጭ አሳልፎ የሚሰጥና ጽንፈኛው ሀይል የሥልጣን ጥማቱን ለማርካት የገባበት ነው” ያሉት ሜ/ጀነራል መሀመድ ተሰማ፤ በአሁኑ ሰዐት ይህንን ውጊያ ለመመከት መላው የፀጥታ ኃይሎች እየተዋጉ ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ ፍልሚያ ላይ ናቸው ብለዋል።
ሠራዊታችን ጽንፈኛውን ኃይል በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ሥር በማዋልና ለህግ በማቅረብ የአካባቢው ሕዝብ ከነበረበት ጭቆና ነፃ ለማውጣት ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም ጀነራሉ ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY