በአዲስ አበባ የሚገኙት ሜጋና ሱር ኮንስትራክሽን በፌደራል ፖሊስ ተከብበው ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው

በአዲስ አበባ የሚገኙት ሜጋና ሱር ኮንስትራክሽን በፌደራል ፖሊስ ተከብበው ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ቦሌ የሚገኙና የጁንታው ቡድን ዋነኛ ንብረት የሆኑ ድርጅቶች በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ እየተደረጉ ነው።

በዚህ ዘመቻ መሠረት በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ የሚገኘው ሜጋ ማተሚያ ቤትና ህንፃ፣ እንዲሁም ከአጠገቡ የቆመው ሱር ኮንስትራክሽን ህንፃ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል።
ከ20 ዓመት በላይ በህወሓት ውስጥ ዋነኛ መሪ ተዋናይ በነበሩት በወ/ሮ አዜብ መስፍን (የመለስ ዜናዊ ባለቤት) ሲመራ የቆየው ሜጋ ከፍተኛ የሆነ ሙስና ሲፈጸም የኖረበትና ጥቂት የጁንታው አባላትና ልጆቻቸው፣ እንዲሁም ዘመዶቻቸው በሀብት ላይ ሀብት ማካበት የቻሉበት፣ ለሀገርና ለሕዝብ ምንም አይነት ፋይዳ ያልነበረው የንግድ ድርጅት ነው።
አሁን ላይ ሀገሪቱን ወደ ሽብር ማዕከል ለማሸጋገር ጦርነት ያወጀው ፈርጣማ ክንድ እንዲኖረው ያቋቋመውና ከ15 ዓመት በፊት 400 ቢሊዮን ብር ካፒታል እንዳለው ከ17 አ በሪፖርተር ጋዜጣ ጠለቅ ያለ ዘገባ የተሠራለት ኤፈርት የተሰኘው የንግድ ተቋም እንዲያንሠራራ ካደረጉት የህወሓት ንብረቶች መሀል ሱር ኮንስትራክሽንና ሜጋ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው።
በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በሽሬ፣ በራያና በተለያዮ የትግራይ ክልል እና ከአማራ ክልል በሚያዋስኑ ሥፍራዎች ለመንገድ ግንባታና ኮንርትራክሽን ሥራ ባስገባቸው ግዙፍ ማሽኖች እየታገዘ ለጁንታው የክፉ ቀን መሸሸጊያ የሚሆኑ ትላልቅ ምሽጎችን ከሁለት አመት በላይ ሲገነባ የነበረው ሱር ኮንስትራክሽን በአዲስ አበባ የነበረውን የድርጅቱን ቢሮ ወደመቀሌ ያዘዋወረው ከሦስት ሳምንት በፊት ነበር።
እነዚህ ሁለት የህወሓት ንብረቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ሙሉ በሙሉ በፌደራል ፖሊሶች እንዲከበቡ የተደረገ ከመሆኑ ባሻገር፤ በባለሙያዎች የታገዘ ጠንካራ ፍተሻ እስኪደረግባቸው ድረስ ወደድርጅቶቹ ግቢና ህንፃ ማንም ሰው እንዳይገባና እንዳይወጣ ተደርጓል።

LEAVE A REPLY