ዳግም መከላከያን የተቀላቀሉት ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ ም/ ኢታ ማዦርነት ሹመት ተሰጣቸው

ዳግም መከላከያን የተቀላቀሉት ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ ም/ ኢታ ማዦርነት ሹመት ተሰጣቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ አዳዲስ ሹመቶች ማፅደቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ይፋ አድርጓል።

ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ያልተጠበቀና አዲስ ሹመት ከተሰጣቸው ሰዎች መሀል በቅርቡ ህወሓትን ለመደምሰስ በሚደረገው ትግል ውስጥ ልምድና ብቃታቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ ጥሪ የቀረበላቸው ሌ/ ጀነራል አበባው ታደሰ ዋነኛው ናቸው።
የጦር ሜዳው ጀግና፣ ብልህና ቆፍጣናው ጀነራል አበባው ታደሰ ያለ እድሜያቸው ጡረታ እንዲወጡ የተደረጉት ከህወሓት ቡድን ጋር ባላቸው ሠፊ ልዮነት ነበር።
የሰሜን  እዝ ጦር አዛዥ ሆነው መከላከያውን የተቀላቀሉትና በአሁኑ ወቅት በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ፍልሚያ ላይ የሚገኙት ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ ዳግም መከላከያ ሠራዊቱን በተቀላቀሉ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የጦር ኃይሎች ም/ኢታ ማዦር ሆነው ተሹመዋል።
በተያያዘ ዜና ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ቦታ ደርበው እንዲሠሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው የተነሱት የለውጡ ቡድን አጋፋሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በመሆን በዶክተር ዐቢይ ተሹመዋል።
በሌላ በኩል ም/ኢታማዦር ሹም የኘበሩት ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም፣ የደህንነት ቢሮውን ሲመሩ የነበሩት ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

LEAVE A REPLY