በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ያሰጋቸው 6ሺኅ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን ሸሹ

በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ያሰጋቸው 6ሺኅ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን ሸሹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በትግራይ ኃይሎችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የሚደረገውን ጦርነት ተከትሎ ከ6ሺኅ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን ሸሹ።
ሮይተርስ የሱዳን ባለሥልጣናት በቀጣይ ቀናት እስከ 200 ሺህ ኢትዮጵያውን ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሊገቡ ይችላሉ ሲሉ ቅድመ ግምት ማስቀመጣቸውን ዘግቧል።
 ወደ ሱዳን ድንበር ተሻግረዋል የተባሉት ስደተኞች ሲቪል ወይም ወታደራዊ ይሁኑ ዘገባው ባይገልፅም፤ የስደተኞቹ ቁጥር ትናንት ማክሰኞ 6ሺኅ መድረሱን የሱዳን የስደተኞች ኮሚሽን ማረጋገጡን አስታውቋል።
 6ሺኅ የሚሆኑ ስደተኞች ወደ ሱዳን የዘለቁት ሉቅዲ፣ ቁዳይማህ እና ሀምዳይት በተባሉ የሱዳን ድንበር አካባቢዎች በኩል ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ ስደተኞችም በአትባራ ወንዝ ዳርቻ ወደ ሱዳን ለመሻገር በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።
የሱዳን ዜና አገልግሎት ከቀናት በፊት የጦርነቱን ማገርሸት ተከትሎ፣ የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በከፊል እንደዘጋ መዘገባቸው አይዘነጋም።
በኢትዮጵያ የሚደረገው ጦርነት ያሳሰበው የሱዳን መንግሥት የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ልዩ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ያሲን ኢብራሂም ይህን ስ በጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በአንክሮ እየተከታተሉት እንደሆነና ሁለቱም ተዋጊ ወገኖች ወደ ሰላምና መረጋጋት እንዲመለሱ መልእክት ማስተላለፋቸው ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY