ቢሾፍቱ በተከሰከሰው ቦይንግ አውሮፕላን ላይ የሞቱ ሰዎች አስከሬን ምስል በትግራይ የተገደሉ አማራዎች...

ቢሾፍቱ በተከሰከሰው ቦይንግ አውሮፕላን ላይ የሞቱ ሰዎች አስከሬን ምስል በትግራይ የተገደሉ አማራዎች ሆኖ እየቀረበ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  በትግራይ ክልልና አካባቢው ሰሞኑን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ላይ የተፈፀመ ብሔር ተኮር ጥቃትን የሚያስመስል የተነሳ እንደሆነ ተረጋገጠ።

ቀደም ሲል መንገደኞችን ጭኖ ወደ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ እያለ ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰውንና ከ150 ሰዎች በላይ የሞቱበትን ቦይንግ 737 ማክስ 8 ምስል አንዳንድ ጽንፈኛ የአማራ ብሔርተኞችና ሀሰተኛ የፌስ ቡክ ባለቤቶች ሲጠቀሙበት ተስተውሏል።
በወቅቱ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የሞቱ ሰዎች አስከሬንንና ያኔ የተነሳውን ፎቶ በትግራይ የተገደሉ የአማራ ክልል ልዮ ኃይሎችና የመከላከያ ጦር አባላት አስከሬን አስመስለው ሰሞኑን በተለያዮ ማኅበራዊ ድኅረ ገጾች ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች በዝተዋል።
ይህን ምሥል ምንም እየተካሄደ ውጊያ ጋር የሚያያ ነገር እንደሌለ የሚያረጋግጡ እውነተኛ መረጃዎች አሁን ላይ እየወጡ መሆናቸውን ተከትሎ ምስሉን በስፋት ለጥፈው ከነበሩ ሰዎች መሀል አብዛኞቹ ቢሰርዙትም፣ ሌላ ዓላማ ያላቸው ደግሞ አሁንም ሀሰተኛ ምስሉን እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

LEAVE A REPLY