ጁንታው ጣልኩት ያለው ጄት ከ3 ዓመት በፊት በኢራንና ሊቢያ ሀሰተኛ ዜና...

ጁንታው ጣልኩት ያለው ጄት ከ3 ዓመት በፊት በኢራንና ሊቢያ ሀሰተኛ ዜና የተሠራጨበት መሆኑ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጁንታው በትግራይ ክልል ከፌደራል መንግሥቱ ጋር እያካሄደ በሚገኘው ውጊያ ላይ “መትቼ ጣልኩት” ሲል የገለፀው የጦር ጄት ፈፅሞ ሀሰተኛ መሆኑ ተረጋገጠ።

ቢቢሲ እንደዘገበው ከሆነ ህወሓት መትቼዋለሁ ሲል የፎከረበት ጄት ከሁለት ዓመት በፊት በኢረራንና ሊቢያም እንዲሁ በውሸት ፕሮፐጋንዳ ዜና የተሠራበት መሆኑን አስታውቋል።
ይህንን ከእውነት የራቀ ዜና በህወሓት ውስጥ የሚገኘው ጁንታ፣ የአምባገነኑ ቡድን በቀቀን የሆኑ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች፣ እንዲሁም ጥቂት ደጋፊዎቻቸው የከሰረ የፖለቲካ ውጤታቸውን ለመሸፋፈን በማኅበራዊ ድኅረ ገጾች ላይ በትግራይ ክልል ተመትቶ ወደቀ የጦር ጄት በማስመሰል ሲቀባበሉት ተስተውሏል።
 “የትግራይ ልዩ ኃይል ከሰማይ ጥቃት እየደረሰበት ነው፤ ልዩ ኃይሉ የኢትዮጵያን የጦር ጄት አውድሞታል፤ ሌሎች ልዩ ኮማንዶ አባላትንም ገድሏል፣ ጦርነቱም እንደቀጠለ ነው” ከሚለው አንድ የፌስ ቡክ ተከታይ በተጨማሪ፤ በርካታ የጁንታው አምላኪዎችች የተለያዮ አስገራሚ ጽሑፎችን ሲያስነብቡም ሰንብተዋል።
እንደዚህ አይነት ሀሰተኛ ጽሑፎች በስፋት ይስተዋሉ እንጂ የቢቢሲ ምርመራ ውጤት “ተመታ” የተባለው የጀት ምሥል ፈፅሞ ከኢትዮጵያ አይደለም ብሏል።
በሪቨርስ ኢሜጅ የፍለጋ ዘዴ ተመሳሳይ ምሥሎች ሌሎች ቦታዎች ተገኝተዋል ያለው ዓለም ዐቀፍ የዜና አውታሩ፤ በሐምሌ 2018 በኢራኑ ፕሬስ ቲቪ ሪፖርት ላይ የሳኡዲ የጦር ጄት በየመን መመታቱን የሚያሳይ ምስል፣ እንዲሁም በግንቦት 2015 የትዊተር ሰሌዳ ምሥል ሚግ 25 ፕሌን በሊቢያ ዚንታን ከተማ አቅራቢያ መውደቁን ያሳያል ብሏል።

LEAVE A REPLY