ገዱ አንዳርጋቸው ከሱዳን ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በካርቱም እየመከሩ ነው

ገዱ አንዳርጋቸው ከሱዳን ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በካርቱም እየመከሩ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልእክት ይዘው ሱዳን መግባታቸው ታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትና በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው የተመደቡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአስቸኳይ ሀገራዊ ጉዳይ ሱዳን መግባታቸውን የሁለቱም ሀገራት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማካሪ ወደ ካርቱም ያቀኑት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌ/ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ለማድረስ እንደሆነም ተሰምቷል።
ሱዳን የገቡት ገዱ አንዳርጋቸው ከሌ/ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ዙርያ በጥልቀት መምከራቸው በመነገር ላይ ነው።

LEAVE A REPLY