የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ከውጭ የሚያስመጡና የሚያርቱ ግብር ከፋዮች ላይ አዲስ መመሪያ...

የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ከውጭ የሚያስመጡና የሚያርቱ ግብር ከፋዮች ላይ አዲስ መመሪያ ወጣ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ከውጭ የሚያስመጡና የሚያመርቱ ግብር ከፋዮች ራሱን የቻለ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስገድደው ጊዜ ለ6 ወር ተራዘመ።
የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁን ተጨማሪ 6 ወር እንዲሰጥ አድርጎ ዛሬ አሻሽሎ ማፅደቁ ተረጋግጧል።
ባለፈው ዓመት በፀደቀው ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ መሠረት ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ለማምረት ወደ ሀገር ለማስገባት ምርቶች ራሱን የቻለ ፈቃድ እንዲያወጡ ግዴታን አስቀምጧል።
አዋጁ በፀደቀ ጊዜ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው ፈቃዱን እንዲያወጡ የ6 ወር ጊዜ ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም፣ ይሁንና በኮቪድ 19 ወረርሽን ምክንያት ታውጆ በቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚመለከታቸውን ሁሉ ሰብስቦ፤ ስለ ኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ አወጣጥና ተያያዥ  ጉዳዮች ላይ  ለመነጋገር ሳይቻል እንደቀረ አዋጁን ለማሻሻል የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በግልፅ አስቀምጧል።

LEAVE A REPLY