ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህወሓት ሹማምንትና የቢዝነስ አጋሮቻቸውእንዳቋቋሙት የሚነገርለት በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ በርካታ የጦር መሣሪያ መገኘቱ ታወቀ።
በአዲስ አበባ ባለው በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የተገኙት የጦር መሣሪያዎች ለሌላ ዓላማ ሊውሉ የተዘጋጁ መሆናቸውን የአዲስ የአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።
ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሣሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ የተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል እጅ የሌሉ ጭምር እንደሆኑም አስረድተዋል።
በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ውስጥ በርካታ የጦር መሣሪያ የተገኘባቸው ሌሎች ድርጅቶችና የባለሀብቶች መኖሪያ ውስጥ መገኘቱ ተሰምቷል።