ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የግል ጥበቃ ኤጀንዎች እንዲታገዱ ተወሰነ።
አንዳንድ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን የመንግሥት እና የግል ተቋማትን የመጠበቅ ዓላማን ወደ ጎን በመተው ከቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት መካከል ለሌላ እኩይ ተግባር የመረጧቸውን በመመልመል፣ በተለያዩ አካላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የደረሰበት መሆኑን ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
እነዚህ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ከ2012 ዓ.ም በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት እና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችን እና የተለያዩ ድርጅቶችን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ መቆየታቸው ተነግሯል።
ከዚህ በተጨማሪም ተቋማቱን እንዲጠብቁበት የታጠቁትን በርካታ የጦር መሣሪያ ይዘው እንደጠፉም ተረጋግጧል ብሏል።
ይህን ተከትሎ የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት የኮ/ል አራንሺ ድርጅት የሆነው “አጋር የጥበቃ አገልግሎት”፣ የህወሓት ቀንደኛ ደጋፊ የነበረችው የጋዜጠኛ ሚሚ ስብሓቱና ቤተሰቦቿ ንብረት የሆነው “ስብሓትና ልጆቹ የጥበቃ አገልግሎት”ን ጨምሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 14 ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ ተወስኗል፦
1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ
2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
5. ኃይሌ ተክላይ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ስ/ማ
6. ክፍሌ ጎሳዬ ሃጎስ እና ወ/ገብርኤል የጥበቃ አገልግሎት ሽርክና /ማ
7. ዮናስ፣ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማ
8. ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
9. ደመላሽ፣ ሃፍቱ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
10. ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማ
11. ዋልታ የጥበቃ የሰው ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
12. ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
13. አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግ/ማ
14. ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ