ኤርትራውያንን ጨምሮ 10 ሺኅ ወታደር እንደማረኩ ዶ/ር ደብረፂዮን ተናገሩ

ኤርትራውያንን ጨምሮ 10 ሺኅ ወታደር እንደማረኩ ዶ/ር ደብረፂዮን ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል መስተዳድር ጦርነቱ የቀጠለ ቢሆንም ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትኄ ሊገኝለት ይገባል ብለዋል።

ትናንት ማታ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ መግለጫ የሰጡት የጁንታው ቡድን መሪ፤   በመቀለ፣ በአዲግራትና በአላማጣ ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ጠቁመው፣ የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ረቡዕ ዕለት በአየር ድብደባ መመታቱን ተከትሎ የትግራይ ከተሞች ጨለማ ውስጥ ለመሰንበት እንደተገደዱ ገልፀዋል።
” አሁንም በተለያዩ አቅጣጫዎች የጦርነት ዝግጅቶች አሉ። ውጊያው ገና ነው፤ ገና ጅምር ነው ” ያሉት ደብረፂዮን፤ የህወሓት ሚሊሻ እስካሁን ከ10 ሺኅ በላይ ወታደሮች እንደማረከና ከእነርሱ ውስጥም  የኤርትራ ወታደሮች ይገኙበታል ሲሉ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY