ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጁንታው ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸውና በሽብር ተግባር ላይ ተሠማርተዋል በሚል የተጠረጠሩ 96 ግለሰቦች ትእዛዝ ወጣባቸው።
የእስር መያዣ ከወጣባቸው መካከል 64ቱ ሲቪሎች ሲሆኑ 32ቱ ደግሞ ወታደራዊ መኮንኖች እንደሆኑና ከመካከላቸውም ሠባት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ታውቋል።
ፖሊስ በከባድ ወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ብሎ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ካወጣባቸው 64 ግለሰቦች መካከል ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር (ሞንጀሪኖ)፣ የቀድሞው አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ ወ/ሮ ኪሪያ ኢብራሂም፣ የቀድሞው የደኅንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አምባሳደር ስዩም መስፍን፣ አቶ አባይ ፀሐዬ፣ አቶ ዘርዓይ አስጎዶም፣ አቶ ስብሀት ነጋ እንደሚገኙበት ታውቋል።
በተመሳሳይ ወንጀሎች ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው ከተጠረጠሩና የእስር መያዣ ከወጣባቸው የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የፖሊስ አባላት መካከልም፤ ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ተስፋዬ፣ ሜ/ጀነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ ተስፋይ፣ ሜ/ጀነራል ብርሃነ ነጋሽ በየነ፣ ብ/ጀነራል ኃ/ሥላሴ ግርማይ ገ/ሚካኤል፣ ብ/ጀነራል ምግበ ኃይለ ወ/አረጋይ፣ ይገኙበታል።