ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በእስረኛ አያያዝና ምርመራ ወቅት በሰዎች ላይ ድብደባና አግባብበት የሌለው ተግባራትን የፈጸሙ የፖሊስ አባላት ከሥራ ገበታቸው እንዲታገዱና በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
በየካ ክፍለ ከተማ የማህበረሰብ ዐቀፍ የፖሊስ አገልግሎት መምሪያ ኮማንደር ባሳዝነው አክሎክ፤ ሁለት የፖሊስ አባላቶች በፈፀሙት የሰብኣዊ መብት ጥሰት እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በቦሌና የካ ፖሊስ መምሪያዎች ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ፣ በርካታ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ደግሞ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።