ባህር ዳርና የጎንደሯ አዘዞ ከተሞች ላይ ሌሊት የሮኬት ጥቃት ተፈጸመባቸው

ባህር ዳርና የጎንደሯ አዘዞ ከተሞች ላይ ሌሊት የሮኬት ጥቃት ተፈጸመባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአማራ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ባሕር ዳርና የጎንደር ከተሞች ላይ የሮኬት ጥቃት እንደተፈጸመ መንግሥት አስታወቀ።

ትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ በክልሉ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚመራው ቡድን በሮኬት ጥቃቱ በአውሮፕላን ማረፊያዎቹ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ ውጭ ከባድ አደጋ አልገጠመም ብሏል።
ማታ 5 ሰዐት (ትናንት) አካባቢ በባሕር ዳር ከፍተኛ የተኩስና የፍንዳታ ድምጽ የተሰማ ሲሆን የክልሉ መንግሥት ስለክስተቱ መግለጫ እስከሰጠበት ደቂቃ በሕዝቡ ዘንድ ድንጋጤ አጋጥሟል።
 በባሕር ዳር ከተማ በተለምዶ መኮድ በሚባለው አካባቢ እና ጎንደር ከተማ አዘዞ አካባቢ እነዚህ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን የገለፀው የአማራ ክልል መንግሥት፤
 ፍንዳታው በጸጥታ ኃይሉ በፍጥነት በቁጥጥር ሥር ውሏል ቢልም በምሽቱ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተከታትለው መሰማታቸውን ቢቢሲ የባህር ዳር ሪፖርተሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
የሮኬት ጥቃቶቹን ተከትሎ ሕዝብ መላ ምቱን ወደ አንድ አቅጣጫ ያስቀመጠ ቢሆንም፤ የአማራ ክልል መንግሥት ግን ፍንዳታው ከትግራይ ክልል መንግሥት (ጁንታው) ጋር ይገናኝ አይገናኝ እየተጣራ እንደሚገኝ ገልጿል።

LEAVE A REPLY