የሮኬት ጥቃቱን ተከትሎ ለጁንታው ከተቀመጠው የ3 ቀን ገደብ በፊት ሠራዊቱ እርምጃ ሊወስድ...

የሮኬት ጥቃቱን ተከትሎ ለጁንታው ከተቀመጠው የ3 ቀን ገደብ በፊት ሠራዊቱ እርምጃ ሊወስድ ይችላል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት ማታ በባህርዳር ከተማና በጎንደር የተወነጨፈውን ሮኬት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያስቀመጡት የሦስት ቀን ወይም 72 ሰዐት የገደብ ጊዜ ሊያጥር ይችላል ተባለ።

ጉዳዮን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ነገ ከተለያዮ መንግሥታዊ ተቋሞች በተለይም ከመከላከያ አካባቢ ያሰባሰበው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሆነ የሮኬት ጥቃቱ በፌደራል መንግሥቱም ሆነ በአማራ ክልል መንግሥት ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ጭሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት የፀጥታ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጣቸውን የጠቆሙ ታማኝ ምንጮቻችን ምናልባትም የትግራይ ልዮ ኃይል አባላት በ3 ቀን ውስጥ እጅ እንዲሰጡ የቀረበው ጥሪ ተቀልብሶ በማንኛውም ሰዐት ሠራዊቱ የማጥቃት እርምጃ ሊወስድ ይችላል ብለዋል።
በመንግሥት በኩል የሮኬት ጥቃቱ በህወሓት ስለመፈጸሙ ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫና ማረጋገጫ ባይሰጥበትም ካለው ሁኔታ አንጻር በአማራ ሕዝብ ላይ የተሞከረው ጥቃት ከጁንታው በመሆኑና ቡድኑም ለጥፋት የተዘጋጀ በመሆኑ ፣ ከዚህ  አኳያ የከፋ አደጋ ሳይደርስ ሠራዊቱ እርምጃ አስቀድሞ ሊወስድ የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ በመነገር ላይ ነው።

LEAVE A REPLY