በኮሮና ለተጎዱ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች የመልሶ ማቋቋሚያ እርዳታ ሊደረግ ነው

በኮሮና ለተጎዱ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች የመልሶ ማቋቋሚያ እርዳታ ሊደረግ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኮቪድ-19 ሳቢያ ለተጎዱ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ለሚደርሱ የማህበረሰብ ክፍሎች የመልሶ ማቋቋሚያ እርዳታ ይደረጋል ተባለ።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝን ምክንያት ለደረሰው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የ20 ሚሊየን 536 ሺኅ 953 ብር ድጋፍ ለ17 የሲቪል ማኅበራት መደረጉም ተሰምቷል።
ከCSSP2 የተገኘውን የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ ሲቪል ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን በሓላፊነት በመቀበል የሚያከፋፍል ሲሆን፤ የተመረጡት የሲቪል ማኅበራት በሰብኣዊ መብት ጥሰት፣ በወረርሽኙ ምክንያት ለተከሰተ ሥራ አጥነት፣ ሴቶች ሕጻናት እና አረጋውያን ላይ በአጠቃላይ በወረርሽኙ ምክንያት የተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚውል እንደሆነም ለመረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY