በጉራ ፈርዳ ያሉ ታጣቂዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንደተቸገረ የደቡብ ክልል አስታወቀ

በጉራ ፈርዳ ያሉ ታጣቂዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንደተቸገረ የደቡብ ክልል አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በደቡብ ክልል እየተንቀሳቀሰ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል እንዳዳገተው የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ የታጠቁ አጥፊዎቸን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የአካባቢ መልክዓ ምድር ስፋት ለመደበቅ እና ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ምቹ በመሆኑ አስቸጋሪነቱ እንደበረታ ነው የተነገረው።
እነዚህ አጥፊዎችን ለመያዝ ፈተና አንደሆነበት የገለፀው የደቡብ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፤ በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ ካሳለፍነው ጥቅምት 18/2013 ጀምሮ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ እስካሁን ድረስ ከ60 በላይ ዜጎች ሕይወታቸው እንዳለፈና እና ከአምስት ሺኅ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንደተፈናቀሉ አረጋግጧል።

LEAVE A REPLY