ጁንታውን መሸሻ የሚያሳጣ ዘመቻ ደመቀ መኮንን በተለያዮ ሀገራት እያካሄዱ ነው

ጁንታውን መሸሻ የሚያሳጣ ዘመቻ ደመቀ መኮንን በተለያዮ ሀገራት እያካሄዱ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ም/ ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው ተባለ።

በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመክፈት የሀገር ክህደት የፈፀመውና ተከታታይ የህገ መንግሥት ጥሰቶችን ሲፈፅም የከረመው የአክራሪውን የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን መንግስት ለህግ ለማቅረብ፣ የህግ የበላይነትን የማስፈን ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑን ተከትሎ የሚሸሹ ኃይሎች ወደ ጎረቤት ሀገራት መጠጊያ እንዳያገኙ የሚያስችል ውስጣዊ ሥራ ላይ ያተኮረ ጉዞ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
 ከሥድሥት በላይ ሀገራትን የሚሸፍነው ጉብኝት መንግሥት በሚሠራው የግንዛቤ ማስጨበጫና የድጋፍ ማግኛ ዘመቻ የጁንታው ቡድን መጠጊያ ሊያጣ ይችላል ተብሏል።

LEAVE A REPLY