ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በጊዜአዊ አስተዳደሩ የፈራረሰው የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም እንደሚደራጅ ገለጹ።
የክልሉ ካቢኔና የዞን አስተዳደርም እንደአዲስ እንደሚዋቀርም የተናገሩት ዶ/ር ሙሉ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች እንዳሉ የሚቀጥሉ መሆኑን ጠቁመው፤ መንግሥት የጀመረውን የህግ ማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ይሠራል ሲሉ ተደምጠዋል።
የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በክልሉ ምንም አይነት የልማት ሥራ አልተሠራም ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ህግ የማስከበሩ ሥራ ሲጠናቀቅ የክልሉን ምጣኔ ሀብት ለመታደግ የልማት ሥራዎች ይጀመራል ተብሏል።