በአዲስ አበባ የሚገኙ የአልኮል ፋብሪካዎች በሞላሰስ እጥረት ምክንያት ማምረት አቆሙ

በአዲስ አበባ የሚገኙ የአልኮል ፋብሪካዎች በሞላሰስ እጥረት ምክንያት ማምረት አቆሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ የሚገኙ የአልኮል ፋብሪካዎች ባጋጠማቸው የሞላሰስ እጥረት ምክንያት ሥራቸውን ለመቀጠል እንቅፋት ሆኖብናል አሉ።
በዚህም የተነሳ የአልኮል ፋብሪካዎቹ  ምርት ለማቆም መገደዳቸውን ይፋ አድርገዋል።
ልዩ አዲስ የአልኮል መጠጦች ኢንዱስትሪ እና መስከረም አልኮል እና ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት በዚሁ የሞላሰስ እጥረት ምክንያት ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆማቸውን አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ግዙፉ ብሔራዊ የአልኮል እና የአረቄ ፋብሪካ በግማሽ ደረጃ፣ ባለ ዛፍ የአልኮል እና የአረቄ ፋብሪካም በሞላሰስ ምክንያት በግማሽ ደረጃ ምርት ለማቆም መገደዳቸው እየተነገረ ነው።
አልኮልና አረቄ ፋብሪካዎቹ ለመጠጥነት ከሚያቀርቡት የአረቄ ምርት ባሻገር ለንጽሕና መጠበቂያነት የሚያመርቱት አልኮል ከወቅቱ አንገብጋቢ የኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ መሆኑ በቀጣይ እጥረት ሊከሰት ይችላል ተብሏል።

LEAVE A REPLY