ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ዐራት ወራት 107 ነጥብ 8 ቢለየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ።
የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ባለፉት ዐራት ወራት የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ17.3 ቢሊየን ብር እድገት ማሳየቱን ይፋ አድርገዋል።
ሚኒስቴሩ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 290 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱንና በአራት ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ካደቀው 104.5 ቢሊየን ብር ከዕቅዱ በላይ መሰብሰብ አረንደተቻለ አስረድተዋል።
የህግ ተገዢነት ደረጃ መሻሻል፣ የተቋሙ ሠራተኛና አመራሮች ቁርጠኝነት መጨመር እና የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች በአራት ወራት መጠናከራቸውን ለገቢ አሰባሰብ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል ነው የተባለው።