የ”ጁንታው”ን ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሠራዊቱ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ነው

የ”ጁንታው”ን ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሠራዊቱ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ ያለው የመከላከያ ሠራዊት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን እየተቀዳጀ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጽ/ቤት አስታወቀ።

በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ከህወሓት ነፃ የወጣ ሲሆን፣ ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን የተባሉት አካባቢዎችም በተመሳሳይ  በሠራዊቱ አማካይነት ነፃ መውጣታቸው ተረጋግጧል።
በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችን እንደፈረሱና ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ በመገሥገሥ ላይ መሆኑን የጠቆመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጽ/ቤት፤ በምዕራብ ግንባር ደግሞ በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አኩስም የሚደረገው ግስጋሴ ቀጥሏል ብሏል።
ከጁንታው ጋር በተደረገው ውጊያ በርካታ መሣሪያዎች ከመማረካቸው በላይ ህወሓት ለክፉ ዓላማው ያሰለፋቸው የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም ታውቋል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የህወሓት ጁንታን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል እየተጓዘ መሆኑን ያመላከተው መረጃ፤ የጁንታው ኃይል የመከላከያ ሠራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቶት ወደኋላ እየሸሸ ቢሆንም የትግራይ ሕዝብን በተሳሳተ ፖለቲካ ለማነሳሳትና ለጥፋት ለመዳረግ በእጅጉ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጿል።

LEAVE A REPLY