ሰበር መረጃ – ከጌታቸው አሰፋ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያድርጉ የነበሩ የደህንነት አባላት...

ሰበር መረጃ – ከጌታቸው አሰፋ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያድርጉ የነበሩ የደህንነት አባላት ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሃገሪቱ የደህንነት ቢሮ ውስጥ እስከከፍተኛ ሱልጣን ይዘው የሚንቀሳቀሱ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት አባላትን መያዙን መስሪያ ቤቱ ነው ያስታወቀው።

ከአቶ ጌታቸው አሰፋ እና ቃሊቲ እስር ቤት ካሉት የወያኔ ደህንነቶች መመሪያ እየተቀበሉ ኢትዮጵያን ሲያተራምሱና አማራን ሲያስጨርሱ የነበሩት ከ20 በላይ የሚሆኑ ባንዳዎች ገቢ ሆነዋል ያለው የደህንነት መስሪያቤት   ስም ዝርዝራቸውን ከሃላፊነታቸው ገር በማያያዝ ይፋ አድርጓል።

1ኛ) በእሱፈቃድ ደጀኔ፦ የአማራ ክልል የዉስጥ ደህንነት ባልደረባ የነበረ ማንኛዉንም ግለሰብ ስልክ እየጠለፈና በGPS እየተከታተለ ሲያስገድል የነበረ፣ በተለይ ከቅማንት ጋር በተያያዘ ከህወሓቶች ጋር በመመሳጠር መረጃ እየተለዋወጠ የብሔር ግጭት ሲያቀጣጥል የነበረ ነው።

2ኛ) እንድሪስ ቶምሳ፦ የሀገር ዉስጥ ደህንነት የምስራቅ ወለጋ ኦነግ ሸኔን ያደራጀ መረጃ በመስጠት ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሳ

3ኛ) መሀመድ ኢብራሂም፦ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የሳይበር ዋና ቢሮ ዳይሬክቶር፤ ማንኛዉንም ግለሰብ ስልክ እየጠለፈና በGPS እየተከታተለ የሚያስገድል በመኖሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ቴሌ ኮሚኒኬሽን እዉቅና ዉጭ የሳተላይት ግንኙነት የሚያደርግ፣ በመኖሪያ ቤቱ የራሱ የሆነ የደህንንት መከታተያ መሳሪያዎችን የነበረው

4ኛ) ቁምላቸዉ ዉብሸት፦ የብሄራዊ ደህንነት የመረጃና ደህንነት ትንተና ሀላፊ የነበረ፤ በደህንነት ቢሮዉ የተገኙ ወንጀሎችን አዛብቶ ያልሆነ መረጃ እየሰጠ ሀገር እንድትተራመስ የሚያደርግ፣ የራሱ የሆነ የሞባይል ሳተላይት ያለዉ

5ኛ) የተቀሩት 19 የደህንነት ሰዎች አማራ በሚኖርባቸዉ አጎራባች ክልሎች ጉራ ፈርዳ፤ ሆሮ ጉድሮ፤ ወለጋ፤ መተከል በጎንደር ቅማንትና አማራ ክልል የሚያተራመሱትን እያወቁ እንዳላወቁ መረጃ እያዛቡ እየተነተኑና መረጃ እየሰጡ ሲያስጨፈጭፉ የነበሩት ናቸው።

LEAVE A REPLY