አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ተወያየ

አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ተወያየ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ መልክ በቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄደ።

የህወሓት ቡድን ተወግዶ ሰላምና ደህንነትን ያረጋገጡ ሥራዎች እንዴት መከወን አለባቸው በሚሉት ጉዳዮች ላይ የመከረው የውይይት መድረኩ፤ የህግ የበላይነትን ከማስከበር አንጻር ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ መሥራት እንዳለበት የሚገልጽ ሐሳብን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አንስተውበታል።
መንግስት እየወሰደ ያለው ህግ የማስከበር እርምጃ ተገቢ እንደሆነም በምክክር መድረኩ የተነሳ ሲሆን፤ በተጨማሪም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሙስናና ከብልሹ አሠራር የፀዱ ሥራዎችን በክልሉ መሥራት እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።

LEAVE A REPLY