ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– 76 ጄኔራሎች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች የሀገር ክህደትን ፈፅመዋል ያለው ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የመያዣ ትዕዛዝ አወጣባቸው።
ወታደራዊ መኮንኖቹ በሀገር መከላከያ ሠራዊት በሥራ ላይ ያሉና በጡረታ የተሰናበቱ ጀኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ህወሓት ጋር በመተባበር የሀገርን ሕልውና አደጋ ላይ ጥለዋል በሚል ለህግ ለማቅረብ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደተቆረጠባቸው የገለጸው ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሕግ ለማቅረብ ጥረት እንደሚደረግም አስታውቋል።
አሁን በፌደራል ፖሊሶችና በደሕንነት አባላት እየታደኑ በመያዝ ላይ ያሉት የጦር መኮንኖች ውስጥ በጡረታ የተገለሉና ከጁንታው ቡድን ጋር በመሆን የሽብር ተግባር እየፈጸሙ መሆናቸው ተገልጿል።