ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ከተሰጡት ኃላፊነቶች አንዱ በክልሉ ሥድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማስቻል እንደሆነ ዶ/ር ሙሉ ነጋ አስታወቀ።
ጁንታው ከተባረረ በኋላ በትግራይ ክልል ሥድስተኛው አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ይደረጋል ያሉት አዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ “ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ሓላፊነቶች አንዱ በምርጫ ቦርድ መርህ መሠረት በክልሉ ሥድሥተኛው ብሔራዊ ምርጫ እንዲከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። ሕዝቡም በነፃነት መሪዎቹን ይመርጣል” ሲሉ ገልፀዋል።
“ህወሓት ሕገ ወጥ ምርጫ ነው ያካሄደው። ይህም በፌደሬሽን ምክር ቤት እውቅና አልተሰጠውም። ስለዚህም የክልሉ ምክር ቤት እውቅና የለውም። በክልሉ አመራር ደረጃ ያለውም እውቅና የለውም” በማለት የተናገሩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ፤ በክልል እና ዞን ደረጃ አዲስ አመራሮች እንደሚሾሙም ከወዲሁ አስታውቀዋል።