ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአሁኑ ሰዐት በመቀለ የሚገኘው የትህነግ ቡድን በአየር ኃይል ጀት እየተደበደበ እንደሚገኝና በየቦታው ያሉ የህወሓት ሹማምንት መከበባቸው ታወቀ።
በኢፌዲሪ መከላከያና የአየር ኃይል ውስጥ የሚገኙ ታማኝ ምንጮች እንደገለፁት ከሆነ ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ መንግስት “ጁንታው” ብሎ የሚጠራው የህዋሃት ቡድን በአየር ኃይሉ መከበቡ ለማወቅ ተችሏል።
የህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተለያዮ የጁነታው አባላት ወደሌላ ቦታ ለመሸሽ ጥረት ማድረጋቸውን የገለጹት ምንጮች በተለይም የጌታቸው ረዳ V8 መኪና ግለሰቡ ክትትሉነና የአየር ጥቃቱን ፈርተው አቁመዋት በሸሹባት ቦታ ላይ በጀት መመታቷን ጠቁቀመዋል።
ከአቶ ጌታቸው ባሻገር የአንድ ጀነራል መኪናም በተመሳሳይ ጥቃት የተፈጸመባት መሆኑን የገለጹት ምንጮች በጥቂት ሰዐታት ውስጥ በርከት ያሉ የጁንታው አባላትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል አልያም ለመደምሰስ የሚያስችል ቦታ ላይ ሠራዊቱ እንደሚገኝ ገልጸዋል።