በኢትዮጵያ በትብብር ለሚተላለፉ የራዲዮ ዝግጅቶች አዲስ መመሪያ ሊወጣ ነው

በኢትዮጵያ በትብብር ለሚተላለፉ የራዲዮ ዝግጅቶች አዲስ መመሪያ ሊወጣ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት አድርገው በኢትዮጵያ ባሉ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች በትብብር የሚዘጋጁ የሬዲዮ ዝግጅቶችን አሠራር አቅጣጫ የሚያሳይ መመሪያ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያወጣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ወንድወሰን አንዱዓለም መመሪያው በውስጡ መቀመጫቸውን ውጭ ሀገር ባደረጉ የመገናኛ ብዙኃን የሚሠሩ የሬዲዮ ፕሮግራሞች በትብብር ሀገር ውስጥ ባሉ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች መተላፍ ይችላሉ አይችሉም የሚለውንና ተጠያቂነታቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ በግልጽ የሚያስቀምጥ ነው ብለዋል።
ኤፍ ኤም ጣቢያዎቹ ከሚያስተላልፉት 18 ሰዐት ውስጥ ምን ያህል ሰዐት ወስደው መሥራት እንደሚችሉ እና ከኤፍ ኤም ጣቢያዎቹ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ አኳያ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው የሚያመላክት እንደሆነም መመሪያው አካቷል ተብሏል።
VOA ፣ DW እና BBC በሀገራችን ባሉ የተለያዮ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢዮዎች ላይ እየተላለፉ መሆኑ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY