ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ዛሬ ሮም ጣሊያን መግባቱ ተሰማ።
አቶ ደመቀ መኮንን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ያቀረቡ ሲሆን፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱንም እግረ መንገዳቸውን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሓላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ የገለጹት ጁሴፔ በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሀገራት ረጅም ዘመን የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ወደ ተሻለ የትብብር ከፍታ ለማድረስ ጠንክረው እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።