ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ላለፉት 27 አመታት ሀገር እና ሕዝብን ሲያምስ የኖረው ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን የመጨረሻ ዘመን እንደተቃረበ አቶ ታዬ ደንደአ ገለፁ።
ቡድኑ በትግራይ ሕዝብ ውስጥ ለመደበቅ ቢሞክርም የትግራይ ሕዝብ ግን ጠልቶታል ያሉት የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ፤ ላለፉት ጥቂት አመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቡድኑን ሲታገል እንደነበርም አስረድተዋል።
ሀገሪቱ የጀመረችውን አዲስ የብልፅግና እና የለውጥ መንገድ ለመቀልበስ ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን የጀመረው እንቅስቃሴ ክፋት የተሞላበት ነው የሚሉት ከፍተኛ አመራሩ፤ የክፋት መንገዱም በሀገራችን ታሪክ ያልታየና አሳፋሪ ጭምር መሆኑን አስረድተዋል።