ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ መዋእለ ነዋይ ፈሶበታል የተባለ ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪዎችን የሚገጣጥም ፋብሪካ ወደ ሥራ መግባቱ ተነገረ።
ኢንቨስትመንት በራቃት ኦሮሚያ፣ አዳማ ከተማ ከሦስት ዓመታት በፊት በተረከበው በ50 ሺኅ ሜትር ስኩዌር ቦታ ላይ የተገነባው ፋብሪካ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በየካቲት ወር 2015፣ የሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ አባል የሆነው ሆራ ትሬዲንግ በሕንድ ሀገር ከሚገኘው ግዙፉ 8 አጃጅ አውቶ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን መገጣጠም ጀምሯል።
ወደ ሥራ የገባው ኩባንያ በ56 ደቂቃ (አንድ ሰዐት ገደማ) 23 ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ መገጣጠም እንደሚችል ተነግሮለታል።