የአውሮፓ ኅብረት የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በህወሓት ላይ በሚወስደው እርምጃ ጣልቃ አልገባም አለ

የአውሮፓ ኅብረት የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በህወሓት ላይ በሚወስደው እርምጃ ጣልቃ አልገባም አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የለኝም አለ።

በተለያዮ ሀገራት የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ መምከራቸው ተሰምቷል።
ኮሚሽነር ጃኔዝ  የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግን የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ለህብረቱ ስትራቴጂያዊ አጋር ሀገር መሆኗንም አስረግጠው ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY