ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ለህወሓት መሪዎችና ኃይሎች የሰጡት ጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ በተቃረበበት በመጨረሻው ሰዐት ዓለም ዐቀፉ ማኅብረሰብ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ አሳሰቡ።
“የወዳጆቻችን ስጋት እና ምክረ ሀሳብ ከግምት እያስገባን፤ በውሳጣዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግን ጥረትን አንቀበልም። ስለዚህም ዓለም ዐቀፉ ማኅብረሰብ ተቀባይነት ከሌላው እና ሕጋዊ ካልሆነ ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ፣ እንዲሁም የዓለም ዐቀፍ ጣልቃ-አለመግባት መሠረታዊ ምርሆዎችን እንዲያከብር በአክብሮት እናሳስባለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰዐታት በኋላ የሚወሰደው እርምጃ የማይቀር መሆኑን አረጋግጠዋል።
ዶ/ር ዐቢይ ለጁንታው ባላት የሰጡት ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ በሚኖረው ወታደራዊ ዘመቻ በርካቶች ስጋት ገብቶናል እያሉ መናገራቸውን ተከትሎ ነው ይሄንን ኮስተር ያለ መልእክት ያስተላለፉት።