ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበርና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭትን በተመለከተ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር እንዲወያዩ የተመረጡት ልዑካን አዲስ አበባ ገቡ።
በኢትዮጵያ መንግሥትና በጁንታው መካከል እየተካሄደ ሦስት ሳምንታት ያስቆጠረው ግጭት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ በተሸጋገረበት ጊዜ እነዚህ ሦስት የቀድሞ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ግጭቱ የሚያበቃበትን መንገድ ለመወያየት ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ተሰምቷል።
ልዑኩ የቀድሞውን የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዮአኪም ቺሳኖ፣ የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ሰርሊፍ ጆንሰንና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝደንት የነበሩትን ጋሌማ ሞትላንቴ የያዘ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግን በትግራይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን ማስከበር ስለሆነ ከህወሓት አመራሮች ጋር ምንም አይነት ድርድር ለማድረግ ፍላጎት እንደሌለ በድጋሚ በይፋ አረጋግጠዋል።