ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ሁለት ብሔራዊ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃዶችን ለመስጠት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ መጠየቂያ ሰነድ ማውጣቱን አስታወቀ።
ውድድሩ ፍትሀዊ እንዲሆን የሚያስችለው ሂደት ተገባዶ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃዶችን ለመስጠት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ መጠየቂያ ሰነድ ማውጣቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ይፋ አድርገዋል።
ጨረታው ለሦስት ወራት እንደሚቆይ እና ከዚህ ቀደም ፍላጎት ያሳዩትን ጨምሮ በርካታ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት እንዲሳተፉ ይደረጋል መባሉን ለማወቅ ተችሏል።