ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሦስት የቀድሞ አፍሪካ መሪዎች በአባልነት የያዘውን ከአፍሪካ ሕብረት የተላከውን ልዑክ ዛሬ ተቀብለው አነጋገሩ።
የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ሰርሊፍ ጆንስን፣ የሞዛምቢክ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆአኪም ቺሳኖንና የደቡብ አፍሪካን የቀድሞ መሪ ካግሊማ ሞታህነቴ ናቸው ከዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር የተነጋገሩት።
መንግሥት ከሁለት ዓመት በላይ የህወሓትን የጥፋት አካሄ በመታገስ ሰላማዊ ጥሪ ሲያደርግ ቢቆይም፣ ህወሓት ግን ይህን ባለመቀበሉ የህግ ማስከበር ዘመቻው እየተካሄደ እንደሚገኝ ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ልዑኩን የላኩት የሕብረቱ ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ መንግሥት እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻና የህወሓት ቡድንን ለፍትህ ለማቅረብ እየተካሄደ ያለውን ተግባር በመረዳታቸው ምስጋና አቅርበዋል።