ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያ እና ቁጥጥር መሥሪያ ቤት (CDC) የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ከመጪው ሰኔ ወር አስቀድሞ ወደ አፍሪካ መምጣቱ ሲበዛ አጠራጣሪ ነው ተባለ።
የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ንኬን ጋሶንግ በአሁኑ ወቅት የተወሰኑ የክትባት ዓይነቶች መልካም ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ መሰማቱ በራሱ ተስፋ ቢሆንም፤ ነገር ግን ከበርቴዎቹ ሀገሮች የራሳቸውን ዜጎች ብቻ ለመክተብ ካቀዱ ለአፍሪካ እጅግ አደገኛ ይሆናል ብለዋል።
ሀያላኑ ሀገራት በሙከራ ደረጃ የሚገኙትን ክትባቶች አስቀድመው እንደተቀራመቷቸው የጠቆሙት ባለሥልጣኑ፤
አፍሪካም የክትባቶቹ ተቋዳሽ እንድትሆን CDC አፍሪካ እንደ ቻይናና ሩሲያ ካሉ ሀገሮች ጋር እየተነጋገረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።