ዶ/ር ደብረፂዮን ለራሳችን ሕልውና ስንል እስከመጨረሻው እንፋለማለን አሉ

ዶ/ር ደብረፂዮን ለራሳችን ሕልውና ስንል እስከመጨረሻው እንፋለማለን አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የ “ጁንታው” ቡድን መከማቻ ሆና የሰነበተችው መቀለ ከተማን መያዝ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ይውላሉ ተብለው የሚጠበቁት የህወሓት አመራሮች አሁንም እጅ አንሰጥም ማለታቸውን ቀጥለዋል።

ለጊዜው የት እንደተደበቁ ያልታወቀው የህወሓት ሊቀመንበርና የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል መቀለ ከተማ በመከላከያ ሠራዊቱ ስለመያዟ አንዳችም ነገር ባይናገሩም፣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለፌደራል መንግሥቱ እጅ የመስጠት ፍላጎት እንደሌላቸው አረጋግጠዋል።
ደብረፂዮን ከተሸሸጉበትተ ቦታ ሆነው ለሮይተርስ በላኩት የጽሑፍ መልእክት (መሴጅ) “ለራሳችን ሕልውና ስንል እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን፤ ፈጽሞ እጅ አንሰጥም” ብለዋል።

LEAVE A REPLY