ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በመቀሌ ከተማ የሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ቁስለኛ መሞላ ታወቀ።
በሆስፒታሉ ወስጥ ተገቢውን ሕክምና ለመስጠት የማቴሪያል እጥረት ያገጠመ መሆኑን የገለጸው ዓለም ዐቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አምቡላንሶች በግጭቱ ሳቢያ የተጎዱና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል እያጓጓዙ መሆናቸውንም ገልጿል።
“80 በመቶው ታካሚዎች በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ ሌሎች ሕክምናዎች ቆመው ለድንገተኛ አደጋ ብቻ አገልግሎት እየተሰጠ ነው” ነው ያሉት የዓለም ዐቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ማሪያ ሶልዳድ፤ “ቁስል ለመስፋት የሚውል መገልገያ፣ ፀረ ተህዋሰ መድኃኒት፣ የሕመም ማስታገሻ እና ሌሎችም መድኃኒቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እያለቁ ነው” ብለዋል።
በመቀሌው አይደር ሆስፒታል የሞቱ ሰዎችን አስክሬን ማቆያ ፕላስቲክኮች እየጨረሱ መሆኑን የጠቆመው ማኅበሩ፤ ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱና እንደሞቱ፣ ተጎጂዎቹ ወታደሮች ይሁኑ ሲቪሎች ከመግለጽ ተቆጥቧል።