ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ ሆን ተብሎ የተቀሰቀሱ 113 ግጭቶች መከሰታቸውን ተነገረ።
ግጭቶቹ ብሔርንና ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ መሆናቸውንና ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እንደተከሰቱ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ በርካታ ሰዎች ከሞቱባቸውና ከፍተኛ ንብረት ከወደመባቸው እነዚህ ግጭቶች ጀርባ የስልጣን የበላይነትን መልሰው ለመያዝ ሲጥሩ የነበሩት የህወሓት አመራሮች መኖራቸውን አረጋግጠዋል።
ከሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ሠፊ የቀውስ ዕቅድ መኖሩን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ዕቅድ ተጨማሪ አስር የሚደርሱ ሌሎች ሰዎች በመግደል፣ ግድያውን የብሔር መልክ በማስያዝ ከባድ ጉዳት የማድረስ እቅድ እንደነበራቸውም አስታውቀዋል።