ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የህወሓት ከሀዲ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃቱ ከመፈጸሙ አስቀድሞ የዕዙ አዛዥ ሆኖ ተብሎ እንዲመረዙ የተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠቆሙ።
‘የሰሜን ዕዝ አዛዥ የነበረው ጀነራል ድሪባ ግጭቱ ከመፈጠሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ስብሰባ ከእነርሱ ጋር ውሎ፣ ምሳ ከበላ በኋላ ታሞ እራሱን ስቶ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ገብቷል” ሲሉ በፓርላማው ፊት ሀቁን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ከጀነራሉ ጋር የነበሩ ሰዎች መርዝ አቅምሰውት የሚል መረጃ መስጠታቸውን፣ ጉዳዮ በሕክምና እስኪጣራ ድረስ እንዲቆይ ታፍኖ መቆየቱን ገልጸዋል።
ጀነራል ድሪባ ባጋጠማቸው ችግር ምክንያት አስካሁን አገግመው ወደሥራቸው ያልተመለሱ በመሆኑ፤ ይህንንም ተከትሎ ጀነራሉን በመተካት የሰሜን ዕዝን የሚመራ ጀነራል ቢመደብም፣ የህወሓት አመራሮች አዲሱን ተሿሚ አንቀበልም ማለታቸውም አይዘነጋም።