ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከዛሬ ኅዳር 22/ 2013 ጀምሮ እንደሚያበቃ አስታወቀ።
የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታኅሣሥ 6/ 2013 እንደሚጠናቀቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በድጋሚ ከወዲሁ ሕብረተሰቡ ይወቅልኝ ብሏል።
ይሁን እንጂ አሁንም በአዲስ አበባ በተለይም የዐሥር ብር ኖቶች በስፋት በሕብረተሰቡ ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ሰሞኑን በተለያዮ የገበያ ማዕከሎች በነጋዴዎችና በተገበያይ መሀል ከፍተኛ ውዝግቦች እየታዮ ይገኛሉ።
ነጋዴዎች በተለይም ከአምስት ቀናት በፊት አሮጌውን ብር ሙሉ ለሙሉ አንቀበልም የሚል አቋም በብዛት ይዘው ታይተዋል።