በተለያዮ አካባቢዎች በሚኖሩ ትግራውያን ላይ የአፀፋ እርምጃ አለመወሰዱ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ያሳያል ተባለ

በተለያዮ አካባቢዎች በሚኖሩ ትግራውያን ላይ የአፀፋ እርምጃ አለመወሰዱ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ያሳያል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በትግራይ ክልል የሚደራጀዉ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አሳታፊ በማድረግ እንዲሠራ ተጠየቀ።

መንግስት ያካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የሀገር ሉአላዊነትን የማስጠበቅ ስለመሆኑ የጠቆሙት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴት) ጸሐፊ አቶ ጊደና መድህን፤ ህገ-ወጡ የህወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶችን ወደቀድሞው ለመመለስ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ከመንግሥትና ከትግራይ ሕዝብ ጋር በመሆን እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
የህወሓት ቡድን የትግራይ ክልል ህዝብ ላይ የፀረ-ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሲዘራ መቆየቱን የጠቆሙት ዋና ጸሐፊው፤ ይህን አስተሳሰብ ለማምከን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊተባበር እንደሚገባ አስታውሰው፣ ጽንፈኛው ቡድን በመከላከያ ሠራዊቱ እና በማይካድራ ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ አንዳችም ችግር አለመድረሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጁንታዉ አባላትና የትግራይ ሕዝብ ያላቸውን ልዩነት ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ያረጋገጠ ነው ሲሉ ለዋልታ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY